ወንድማችን ይቅርታ ጠይቋል፤ ይሁን እንጂ ይቅርታዬ ለተሳዳቢዎቼ አይደለም በማለት የራሱን አቋም በግልጽ አስቀምጧል። ከዚህም በላይ ነገሮችን ወቅታዊ ከሆኑ የሀገር ጉዳዮች፣ ስፖርት እና ከሃይማኖት ጋር አላግባብ አቆራኝቶ መቀየር ፍጹም ተቀባይነት የሌለው አደገኛ አካሄድ መሆኑን በአጽንኦት መሰክሯል።
ከሰሞኑ የስፖርት የቦክስ ውድድሮች ጭምር ሃይማኖታዊ መልክ ተሰጥቷቸው መታየቱ ይታወሳል።
እኛም የቀቤና ህዝብ ሕዝብንና ሃይማኖትን ለተለያዩ አላማዎች ማዋሃድ እና ስፖርትን ወደ ሌላ መረን የለቀቀ አቅጣጫ መውሰድ የባህልም ሆነ የሞራል ውድቀት መሆኑን እናምናለን። ይቅርታ መጠየቅ መልካም ቢሆንም፣ የሀገርን ሰላም እና የጋራ እሴቶች የሚፈትኑ እንዲህ ያሉ አካሄዶች ግን ሁልጊዜም ሊወገዙ ይገባል።
ሀይማኖትና ስፖርት የየራሳቸው ቦታ አላቸው፤ ድንበር ማለፍ ግን ፍጹም አይቻልም!
Kebena YouTube
(አቢንሲ ገለጢናም)
ወደ ቀቤና ዩቲዩብ ቻናል መንፈስን በሚያንፁ ገጾች ላይ እንኳን በደህና መጡ!
የቀቤናን ልዩ ባህልና ወጎች በውበት የሚያንፀባርቁ ልዩ ይዘቶችን እንሰጣለን። ባህላዊ ዜማዎች፣ ድንቅ ታሪኮች፣ ልዩ ፕሮግራሞች እና ወቅታዊ መረጃዎች እዚህ ይገኛሉ።
ባህላችንን ለመጠበቅ ፎሎ እና ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
እናመሰግናለን!
ለዚሁ ነበር ወይኔ ሴዶ በቀሉ በቀለችብሽ!
አዝኛለሁ😭
አባይ ቲቪ 12 ሰዓት ያለን በፈረንጆቹ ነበርዴ🤔
ምድር በነ ሴዶ ቦክስ ኪን ስትሞቅ፣ ሰማይ ደግሞ በወዳጃችን በነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ሶለዋት ይደምቃል። ለሁሉም እንንቀሳቀስ፤ ለዚህች የተባረከች ለይል ልባችንን ለሶለዋትም እንስጥ!
ሶሉ ዓለል ሀቢብ! ✨
25/08/2026
የቀቤና ሕዝብ ታላቅ ኩራትና የዕውቀት ማዕከል የሆነው የፍቃዶ ሀድራ፣ የ1ሺህ 501ኛው የነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) መውሊድ በዓልን በድምቀት እያከበረ ይገኛል። በዚህ ታሪካዊ ዕለት የቀቤናን ማህበረሰብ በዕውቀትና በሞራል ለመቅረጽ አርአያነታቸው የላቀ የነበረውን የሰይድ ጀማሉዲንን የላቀ አስተዋጽኦ ልናስታውስ ይገባል።
ሰይድ ጀማሉዲን ለቀቤና ሕዝብ የነበራቸው ልዩ አሻራ የፍቃዶ ሀድራን እንደ መሠረታዊ የእስልምና እምነት ትምህርት መስጫ እና ማህበረሰቡን የሚያቀራርብ የሰላም ምንጭ አድርጎ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ነበር። ማህበረሰቡ በመረዳዳት፣ በመተዛዘን እና በአንድነት እንዲቆም በማድረግ ረገድ የነበራቸው አርአያነት ትውልዱን የገነባ ሲሆን፣ ትውልዱ ከራስ ወዳድነት ወጥቶ ለህዝብ የሚጠቅም መልካም እሴት እንዲላበስ ትልቅ መሠረት ጥለዋል።
በዚህ አጋጣሚ ሰይድ ጀማሉዲን ያስተማሩት ትምህርትና አባባል ዛሬም ለኛ ትልቅ ትምህርት ይሆናል። ዛፍ ጥላ የሚሆነው ለሌሎች እንጂ ለራሱ አይደለም፤ የሰው ልጅም ዋጋ የሚለካው ለወገኑና ለህብረተሰቡ ባበረከተው መልካም አሻራ ልክ ነው ይሉ ነበር። ስለዚህ ዛሬ በምንከብረው መውሊድ ዕለት፣ ከእሳቸው የትምህርት ማዕከል የምንወስደው ትልቁ ትምህርት መከባበርን፣ መደጋገፍን እና የህዝባችንን አንድነት ከፍ አድርጎ ማስቀደም ይገባል።
🔥 ድንቅ ታሪክ! የቀቤና ኩራት የሆኑት አንበሳው ሼኻችን በአንዋር መስጂድ መውሊዱን ሲያጧጡፉት! 🔥
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት የዘቢሞላ ሀድራ ፍሬ ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጂድ መውሊድ በታላቅ ድምቀትና መንፈሳዊ ስሜት ተከብሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን ለአቅመ ደካሞች የተደረገው የምግብ ማብላት ስነ-ሰርዓትም እጅግ የሚያስመሰግን ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲህ በድምቀት የሚከበረውንና የሕዝበ ሙስሊሙን አንዱ ታላቅ እሴት የሆነውን ይህንን ዕለት፣ የክልል መጅሊሶችና ኃላፊዎች ዝምታ በመምረጥ ቸል ማለታቸው ፈጽሞ የሚታለፍ አይደለም። ሕዝቡ በበዓል ደስታ ውስጥ ባለበት ሰዓት ድምፅ ማጥፋትና ማዳፈን ተገቢ አለመሆኑን እየገለጽን!
Telegram👇👇
https://t.me/Kebena_youtube
24/08/2026
ለቀቤና ዩቲዩብ ሚዲያ ተከታዮችና ለመላው የቀቤና ህዝብ በሙሉ!❤❤
የዓለማት ብርሃን የሆነው የታላቁ ነብይ የሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል (መውሊድ) ሲከበር የደስታችን ልክ የለውም። እንኳን አደረሳችሁ! 💚✨
የቀቤና መሬት የትናንት ትውልድ ትዝታ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ ዘቢሞላ ሀድራ፣ ቀጥበሬ ሀድራ፣ ዳንሺይ ሀድራ፣ ፍቃዶ ሀድራ፣ ሩሙጋ ሀድራ፣ ፈረጀቴ ሀድራ እና ሌሎችም ታሪካዊ ሀድራዎች የጥበብ፣ የዚክርና የኑር ማዕከላት የረገጡባት የክብር ምድር ናት። እነዚህ የዕውቀትና የእምነት ማማዎች የኛ ማንነት፣ የዕድሜ ልክ ግዛቶቻችንና የኩራታችን ዮሮዎች ናቸው።
ዛሬ ላይ ሆነን ሐቅን ሳንስት መናገር ያለብን አንዱ እውነት አለ፦ ዛሬ ላይ ሆነው የአባቶቻችንን የዘመን አቆጣጠርና የሀድራ መንገድ እያጠላሉ፣ ነገ በራሳቸው መነጽር ታሪካችን እያሉ ሊያስጎብኙንና ሊያስተዋውቁን የሚሞጡ ወገኖች አሉ። ነገር ግን የሰው ጌጥ ለባጩ አያምርበትም፤ የሰው እህል በልቶ የራሱን ግቢ እንደማመስገን ነው! ዛሬ ላይ ቆመው የጥንት አባቶቻችንን መድረኮች አጥልፈው ለመስራት የሚሯሯጡ አካላት፣ የሌለ ታሪክን ፍለጋ የሚባዝኑ የባዕድ ቱባዎች እንጂ የባለቤት ዓይን የላቸውም።
የአባቶቼን የደም ስርና የረጅም ዘመን የሐድራ ታሪክ ጠልፌ፣ በውጭ ሰዎች ቅኝትና አዲስ ትርክት ተሸንፌ የናንተን መንገድ ፈጽሞ አልቀበም። የአባቶቻችንን ታሪክና እሴት አንክዶ፣ የጥንት ገድሎቻችንን አጥልሎ ወደ ኋላ የሚመልሰኝ ኃይል የለም!
መርሃባ ያ ረሱለላህ! የነብዩ ፍቅር የሞላባቸው የጥንቶቹ ሀድራዎቻችንና የአባቶቻችን መንገድ ለዘላለም በክብር ይኖራል! 🌙✨
👇👇
Kebena YouTube
የቀቤና ጸጋዎች 🌿✨
በገጣሚ ሙባሪክ ያሲን ድንቅ ብዕር የተቃኘውና የቀቤና ልዩ ወረዳን የተፈጥሮ ውበት፣ መንፈሳዊ ታሪክ፣ የሀድራዎች በረከት እንዲሁም የህዝቡን እንግዳ ተቀባይነትና አብሮነት የሚያወድሰው "የቀቤና ጸጋዎች" የተሰኘው ድቅድቅ ግጥም ቀርቦላችኋል።
ከወልቂጤ ባህል ማዕከል እስከ ጬካ ተራራ፣ ከዘቢሞላና ቀጥበሬ ሀድራዎች እስከ ደቀንሺ ፏፏቴና ዋቤ ወንዝ ድረስ ያሉትን ድንቅ እሴቶች በጋራ እንቃኝ!
ተመልክታችሁ ለወገናችን ሼር ማድረጋችሁን አትርሱ። 👍❤️
Telegram👇
https://t.me/Kebena_youtube
✨ የልጅዎን የወደፊት ተስፋ በፅኑ መሰረት ያንፁ! ✨
🏫 የነገ ትውልድ ህፃናት መዋያና ኬጂ ትምህርት ቤት የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጀምሯል!
ለምን የነገ ትውልድ?
✅ በጨዋታና በፈጠራ የታገዘ ዘመናዊ ትምህርት
✅ ፍቅራዊና ልምድ ያላቸው መምህራን
✅ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንፁህና አየር አየር ያለው የመማሪያ ግቢ
✅ ለህፃናት እድገት ምቹ የሆኑ ዘመናዊ የመጫወቻ ቁሳቁሶች
አድራሻ፦ ወልቂጤ ከተማ ካምፕ አደባባይ በጅማ መስመር 150 ሜትር ገባ ብሎ!
📞 ለበለጠ መረጃ እና ለመመዝገብ አሁኑኑ ይደውሉልን!
0936134859
0950169765
ማረቆዎች የታላችሁ!
👇Follow እኛ አንድ ነን👍❤
Kebena YouTube
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Address
Wolkite