15/04/2026
Congratulations 🎉🎊🎈🍾 Halaba FC @ #@@
Official page of wolkite city football club ወልቂጤ
15/04/2026
Congratulations 🎉🎊🎈🍾 Halaba FC @ #@@
ተናግረን ነበር ሰሚ ያጣ ጩኸት
27/03/2024
የሀዘን ዜና ! ኢትዮጵያ ኮከብ ተጨዋቿን አጣች!
አዲሱ ሙሽራ ማረፉ ተሰምቷል !
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የባህርዳር ከነማው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች አለልኝ አዘነ በድንገት ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
በቅርቡ የጋብቻ ስነ ስርዓቱን በቤተክርስቲያን የፈፀመው አዲሱ ሙሽራ ድንገት ዛሬ ለሊት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል ።
ለአርባምንጭ ታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው፤ ለሀዋሳ ከተማና አሁን ለባህርዳር ከተማ በሊጉ የሚጫወተው አለልኝ አዘነ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ጥሪ ተደርጎለት አገልግሎት ሰጥቷል።
አመለ ሸጋው ተጨዋች አለልኝ አዘነ ላለፉት ሁለት አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ክለቡንና ሀገሩን እያገለገለ የሚገኝ ወጣት ተጨዋች ነበር።
ወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በአለልኝ አዘነ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።
09/03/2024
የወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ የገቢ ማሰባሰቢያ ጎፈንድሚ ተከፍቷል። የምትችሉትን ድጋፋችሁ እንድታደርጉለት እንጠይቃለን።
ለወጣት ስፓስተኛ ወንድሙ ቱርጋ እንድረስለት, organized by Hunlachew Sebgaze ወጣቱ ወንድማችንን እንታደግ ወጣት ስፖርተኛ ወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ ከልጅነቱ እስከ ዕውቀቱ በወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ውስጥ ሲ… Hunlachew Sebgaze needs your support for ለወጣት ስፓስተኛ .....
08/03/2024
ባለዉለታዉ ወጣት ወንድሙ ቱርጋ ሁሉም ይድረሰለት!!
ወጣት ስፖርተኛ ወንድማችን ወንድሙ ቱርጋ ከልጅነቱ እስከ ዕውቀቱ በወልቂጤ ከተማ ቅርጫት ኳስ ቡድን ውስጥ ሲጫወት የነበረ ሲሆን በነበረው ከፍተኛ አቅም ጉራጌ ዞንን፣ የቀድሞው ደቡብ ክልልን እና የኢትዮጲያ ብሄራዊ ቡድን ቅርጫት ኳስ በመወከል ህዝብንና ሀገሩን ሲያገለግል ቆይቷል፡፡
በተጨማሪም ታዳጊ ልጆችን ተተኪ ለማፍራት ሲያሰለጥን ነበር፡፡
ነገር ግን በልምምድ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ጉዳት ምክንያት የቀኝ እጁ ታሞ ላለፉት አራት አመታት ሲንገላታና ያለውን አሟጦ 300 000 ብር በቤተሰቡ ወጪ በማድረግ ህክምናውን እየተከታተለ ቢቆይም የእጁ ጉዳት ከባድ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነርቩ የተጎዳ በመሆኑ አሁን ላይ ከባድ የነርቭ ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡
ስለሆነም አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ህክምና የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን በሳምንት 40,000 ብር የህክምና ወጪ እያወጣ ሲሆን ህክምናውም በፍጥነት ማገኝት ስለሚኖርበት ለህክምናው ከ 3,000,000 ብር ( ሶስት ሚሊዮን ብር) በላይ ስለሚያስፈልገን ይህ ወጪ ደግሞ በቤተሰቡ አቅም ሊሸፈን የማይችል በመሆኑ በፍጥነት ማግኝት አለበት፡፡
ህክምና ማግኝት ካልቻለ ህይወቱ ላይ አደጋ ሊያስከትልበት እንደሚችል ሀኪሞች ያሳወቁን ሲሆን ህይወቱን ለመታደግ የእርሶን እርዳታ ስለ ሚያስፈልገን ድጋፍ እንዲያደርጉልን ስንል በፈጣሪ ስም እንለምኖታለን።
መርዳት የምትፈልጉ በኮሚቴዎች በተከፈቱ አካዉንቶች ድጋፍ አድርጉ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000612297677
ወይም
አቢሲንያ ባንክ 179112 345
( በአስተባባሪ ኮሚቴ አካዉንት የተከፈተ ነዉና ሁሉም ይደግፈዉ ይህ ብርቱ ወጣት ትልቀ ባለዉለታችን ነዉ።
ስልክ
0920960849 ( ሌክሲ ቱርጋ )
+251911398020 ( ባሀሩ ተካ)
+251920967710 (ዘመዴ በቀሉ)
ሰጪ እጆች በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ቦታ አላቸዉ።
ኑሬ ረጋሳ
07/03/2024
ክለቡ ከውጤት ደረጃ እና ከደጋፊው ልብ ውስጥ እየሸሸ እና እየወረደ እንዳይሄድ ልንታደገው ይገባል።
ከዚህ በፊት ባሳለፍናቸው የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ታሪክ ውስጥ በፌክ ፌስቡክ አካውንት ጋጋታ ፤ ስድብ ፤ ወከባ ፤ ጠርዝ በሌለው ወቀሳ...ይወከብ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።ነገር ግን ያ ሁሉ ልክ ያልሆኑ ኢ ሥነ ምግባራዊ ነገሮች ዛሬ ላይ አንዳቸውም የሉም።።ምክንያቱ ደግሞ ግልፅ ነው.......ይህ ማለት ክለቡን ለሚመሩት አካሎች ተረጋግተው እንዲመሩ ዕድል የሰጠ ነው።
አሁን ላይ ክለቡ በሁለት መንገዶች ችግር ውስጥ ነው ።አንደኛ በውድድሩ ውስጥ ካለው ደረጃ መውረድ ሁለተኛ ደግሞ በደጋፊው ልብ ውስጥ ካለው ደረጃ መውረድ ነው።
በሁለቱ መንገዶች ችግር ውስጥ ነው ሊባል ይችላል።
ክለቡ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ከክልል እስከ ዞን ባሉ የመንግስት አካላት እየታገዘ እና እየተደገፈ ቢገኝም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት የውጤት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ሆኗል።
መታወቅ ያለበት ዘንድሮ ከብዙ ክለቦች በተሻለ ወልቂጤ ለተጫዋቾች ደሞዝ ይከፍላል። ነገር ግን ከውጤት ቀውስ መውጣት አልቻለም።
ታድያ ችግሩ ምኑ ጋር ነው ??መፍትሔውስ ምንድነው??? ማንን ነው የምንጠይቀው ??ማንንስ ነው የምንወቅስው?? ከማን ጋር እንነጋገር?????????? የሚሉ ጥያቄዎች እየበዙ በመምጣታቸው ክለቡን የሚመሩት አካላት ለነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት እና ለክለቡም መፍትሔ ሊሰጡት ይገባል።
14/02/2024
ኢትዮጵያ በመሠረተችው የአፍሪካ እግር ኳስ መሪነት ክብሯ ለመመለስ መልካሙ እርምጃ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ መስራች ሆና ወደ ፊት የመጣች ቀዳሚት ሐገር ብትሆንም ላለፉት አስርት አመታት ከሜዳ ውስጥ ሆነ ከሜዳ ውጭ ይህንን መሪነቷን ማስቀጠል አልቻለችም ።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በእግር ኳሱ በኢንተርናሽናል አልቢተሮቿ ባሞላክ ተሰማ እና ሊዲያ ታፈሰ እንዲሁም በኤሊት ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በኳሱ በተሻለ ሁኔታ ለመጠራት በቅታለች።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እንደ ተቋም መልካም የሚባል እድገትን ማሳየት የቻሉት አቶ ኢሳያስ ጅራ የካፍ የስራአስፈፃሚ አባል መሆን በቅርብ በእግር ኳሱ መሪነት እንደሐገር ከተገኙ የመሪነት ቦታወች መልካሙ ዜና ሆኗል ።
በእግር ኳሱ የእርስ በእርስ ግንኙነት ስራወች ላይ መልካም ተሞክሮን ማሳካት የቻሉት የፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት የስራአስፈፃሚ አባል መሆናቸው ለሐገራችን እግር ኳስ ጥሩ ተሞክሮ እና ከሌሎች ጋር አብሮ የመስራት እድልን እንደሚያጎናፅፍ ተስፋ እናደርጋለን ።
እንኳን ደስ አልዎት አቶ ኢሳያስ ጅራ
07/02/2024