Mister-ማን ዩናይትድ

Mister-ማን ዩናይትድ

Share

Only Man United 🇪🇹

06/09/2026

‼️እመኑኝ ካሪክ ለራሽፎርድ ብሎ በዚህ አሰላለፉ ከቀጠለ የምናጣቸው ተጫዋቾች!!
ኩንሀ፣
ሴስኮ

06/09/2026

የማንችስተር ዩናይትድ አዙሪት" (The United Cycle)

1. ኦሌ ጉናር ሶልሻየር

ይህ አዙሪት በጉልህ የታየው በሶልሻየር ወቅት ነው።

ሹመት (December 2018)፦ ጆዜ ሞሪንሆ ሲባረሩ ክለቡ የቀድሞ አጥቂውን ሶልሻየርን በጊዜያዊነት ቀጠረ።

የመጀመሪያው ለውጥ፦ ሶልሻየር እንደመጣ ቡድኑ ላይ ትልቅ መነቃቃት ፈጠረ። በተለይ ፒኤስጂን (PSG) በሻምፒዮንስ ሊግ አስገራሚ መመለስ (Comeback) አድርጎ ሲያሸንፍ ደጋፊውና ቦርዱ በደስታ ፈነጠዙ።

ቋሚ መሆን፦ ክለቡ በስሜት ተገፋፍቶ March 2019 የሶስት ዓመት ቋሚ ውል ሰጠው።

ስንብት (November 2021)፦ ቋሚ ከሆነ በኋላ ቡድኑ መደበኛ ብቃቱን ማጣት ጀመረ። ምንም ዋንጫ ሳይበላ በውጤት ማሽቆልቆል ምክንያት ተባረረ።

2. ሩድ ቫን ኒስትልሮይ (አጭሩ ስኬት)

ሹመት (October 2024)፦ ኤሪክ ቴን ሃግ ሲባረር ሌላኛው የቀድሞ ድንቅ አጥቂ ቫን ኒስትልሮይ በጊዜያዊነት መራቸው።

ለውጡ፦ በአሰልጣኝነት በቆየባቸው 4 ጨዋታዎች 3ቱን አሸንፎ 1 አቻ በመውጣት ቡድኑን አነቃቃ። ነገር ግን ዩናይትድ አስቀድሞ ከሩበን አሞሪም ጋር ስለተስማማ እሱ በቋሚነት ሳይቀጥል ቀረ።

3. ማይክል ካሪክ (አዲሱ ታሪክ)

ካሪክ የዚህ አዙሪት የቅርብ ጊዜ ማሳያ ነው።

የመጀመሪያ ሹመት (November 2021)፦ ሶልሻየር ሲባረር ለ3 ጨዋታዎች መርቶ ሳይሸነፍ ለራንግኒክ አስረከበ።

ሁለተኛ ሹመት (January 2026)፦ ሩበን አሞሪም ከተሰናበተ በኋላ (ከዳረን ፍሌቸር አጭር ቆይታ በመቀጠል) ካሪክ ዳግም ቡድኑን በጊዜያዊነት ተረከበ።

ለውጥና ቋሚ መሆን (May 2026)፦ ካሪክ ቡድኑን ተረክቦ አስደናቂ ለውጥ በማምጣት (ከ16 ጨዋታዎች 11ዱን አሸንፎ) ዩናይትድን ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ መለሰ። በዚህም ምክንያት ክለቡ እምነት ጥሎበት የ2 ዓመት ቋሚ ውል ሰጥቶታል::

ለምንድነው ይህ አዙሪት የሚደጋገመው?

1. ቀውስ: ትልቅ ስም ያለው አሰልጣኝ (ለምሳሌ ሞሪንሆ፣ ቴን ሀግ፣ አሞሪም) ከቦርዱ ወይም ከተጫዋቾች ጋር ተጣልቶ ይባረራል።

2. ናፍቆት: ክለቡ "የፈርጉሰንን መንፈስ" እና የድሮውን የማንችስተር ባህል የሚያውቅ የቀድሞ ተጫዋች ያመጣል።

3. መነቃቃት:ተጫዋቾች ከአዲሱ ሰው ጋር አዲስ ተነሳሽነት አሳይተው ጥቂት ጨዋታዎችን በተከታታይ ያሸንፋሉ (Manager Bounce)።

4. መቸኮልቦርዱ የረጅም ጊዜ እቅድ ከማውጣት ይልቅ በደጋፊው ግፊትና በጊዜያዊ ውጤት ተደስቶ አሰልጣኙን ቋሚ ያደርጋል።

5. ውድቀት:ስሜቱ ሲበርድ የታክቲክ ክፍተቶችና የቡድኑ መዋቅራዊ ችግሮች ጎልተው ይወጡና አሰልጣኙ ይባረራል።

ይህ የአሰልጣኝ ቅጥር ሂደት ማንችስተር ዩናይትድ ላለፉት ዓመታት ከስሜታዊነት ያልተላቀቀ የአመራር ዘይቤ እንደነበረው ትልቅ ማሳያ ነው።

በአሁኑ ወቅት ክለቡን በቋሚነት እየመራ ያለው ማይክል ካሪክ ይህንን አዙሪት ሰብሮ ለረጅም ጊዜ ስኬታማ መሆን አለመሆኑን ደጋፊው በጉጉት የሚጠብቀው ጉዳይ ነው።

06/09/2026

ካሪክ አምና የሰራለትን የኩኛ-ሴስኮ-ምቤሞ ጥምረት ለምን መንካት ፈለገ እስቲ አስረዱኝ???ራሽፎርድን ለማስደሰት ካልሆነ በቀር!!

06/09/2026

እንዴት ነበር ጨዋታው?የኩኛ በማይፈልገው ቦታ ማሰለፍ!ለራሽፎርድ ብሎ ሴስኮን ቤንች ማረጉ!በዚህ ከቀጠለ መልበሻ ክፍሉን ያጣዋል!!ገዢ አቶ የቀረውን Bomb Squad ራሽፎርድ እንግሊዛዊ በመሆኑ አምና የነበረውን የቡድኑን ቅርፅ አሳጥጦታል

05/09/2026

አሁን ባለው ሪከርድ አቋሙን ጠብቆ ከቀጠለ ሮናልዶ ላይ ለመድረስ 15 አመት ይፈጅበታል!!Goat ነው ስንል በምክንያት ነው

05/09/2026

ኧረ የቶትሽ ነገር እያሳሰበኝ ነው🤔

05/09/2026

👌👌👌ዝም ነው

04/09/2026

‼️የማንችስተር ዩናይትድ ውስጣዊ ምንጮች እንደገለጹት፣ በርካታ ተጫዋቾች በዚህ ክረምት በማይክል ካሪክ አዳዲስ የልምምድ ዘዴዎች ላይ አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል።Indykaila

​የእሱ አቀራረብ ቡድኑ በቁጥር በርከት ብሎ እና በይበልጥ በቁርጠኝነት ማጥቃት እንዲችል እየረዳው ነው የሚል እምነት በክለቡ ውስጥ እየጨመረ መጥቷል፤ በዚህም የተነሳ ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እየታዩ ይገኛሉ።

04/09/2026

የማንችስተር ዩናይትድ የቻምፒዮንስ ሊግ ስብስብ ይፋ ሆኗል!

​ግብ ጠባቂዎች፡
ሰኔ ላሜንስ፣ ካርል ዳርሎ፣ ቶም ሂተን፣ ደርሞት ሚ

​ተከላካዮች፡ዲዮጎ ዳሎት፣ ኑሰር ማዝራዊ፣ ማቲያስ ዲ ሊግት፣ ሃሪ ማጓየር፣ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ፣ ፓትሪክ ዶርጉ፣ ሉክ ሾው፣ አይደን ሄቨን

​አማካዮች፡ሜሶን ማውንት፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ፣ ዩሪ ቲሌማንስ፣ አንድሬ ሳንቶስ፣ ካርሎስ ባሌባ፣ ማኑኤል ኢጋርቴ፣

​አጥቂዎች፡ማርከስ ራሽፎርድ፣ ማቲያስ ኩንሃ፣ ብሪያን ምቤሞ፣ ቤንጃሚን ሴስኮ፣ ታይናን ቶምፕሰን፣ አማድ ዲያሎ፣ ጆሹዋ ዚርክዚ

ኮቢ ማይኑ እና ሌኒ ዮሮ በክለቡ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት የቆዩ ከ21 ዓመት በታች ተጫዋቾች በመሆናቸው መመዝገብ አይጠበቅባቸውም

03/09/2026

ብሩኖ ፈርናንዴዝ የሶፋስኮር (Sofascore) የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡🏅✨

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in London?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Manchester
London