ኢ ት ዮ

ኢ ት ዮ

Share

Evrye thing is nathng all of can passe time all of simple my gode

03/05/2022

Eid mub
arik

23/03/2019

#ወዳጄ📶
🔹ተስፋህ በፈጣሪ ከሆነ መቼም ቢሆን አትወድቅም
▫በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ካጣኸው በኃላ ይቆጭሀልና
🔸ባጣኸውም ነገር አትበሳጭ የተሻለውን ፈጣሪ ይሰጥሀልና
🔹የበደለህን ይቅር በል አምላክ ይቅር ባዮችን ይወዳልና
▫ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ጌታህን አመስግን እርሱ አመስጋኞችን ይወዳልና
🔸ባለህ ነገር አመስግን ፈጣሪን ይጨምርልሀልና
🔹በወንድምህ ውድቀት አትደሰት ነገ ሌላ ቀን ነው ▫ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና
🔸የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ እርሱ ካንተ ጋር ነውና
🔹ድሆችን እርዳ ሰደቃ/ምፅዋት ወንጀልን ታብሳለችና
▫ሰወችን አትመቃኝ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለችና
🔸ወደ ፈጣሪህ ተጠጋ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነውና
🔹አምላክህን አፍቅረው እሱ የእውነተኛ ፍቅር ባለቤት ነውና
🔸ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ ነውና
🔹ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም ውሳኔው የፈጣሪ ነውና
🔸በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አምላክ ከታጋሾች ጋር ነውና
🔹ለሁሉም ነገር አትቸኩል ችኮላ የሸይጧን ነውና
▫አትበሳጭ ብስጭት የሸይጧንን በር ትከፍታለችና
🔸የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ ያስታውስሀልና።

05/08/2018

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ዓርማዬ
ልጄ ብለሽ ጥሪኝ አለሁ ኢትዮጵያዬ
ስቀሉት ዓርማዬን እንደ ማርያም ልጅ
ስቀሉት ዓርማዬን አውጡና እንጨት ላይ
ፍቅር ከሰው ሁሉ ከፍ ብሎ እንዲታይ !
አንድ ሀገር አንድ ባንዲራ አከተመ

27/07/2018
27/02/2018

"ያልተፈታ ህልም"
ክፍል
(፡AN)2

እኔም እንደ አብዛኛው ሰው ተፈጥሮን አደንቃለሁ ዛሬ በጠዋት ነው የነቃሁት ቀኑ ደስ ይላል ፀሀይ በትንሹ እንደመውጣት እያለች ነው እኔም በትንሹ የወጣችውን ፀሀይ ለመሞቅ ፀሀይዋ ወደ አለችበት አቅጣጫ በእንጨት ከተሰራው ትንሹ ወንበር ላይ ተቀምጬ ፀሀይ እየሞኩ ነው፡፡ የተወሰነ እንደሞኩኝ ሰውነቴ መነቃቃት ሲጀምር ከ እቤት በኩል በተደጋጋሚ ሰሚር .... ሰሚር እያለች በምትጠራኝ በ እማዬ ድምፅ ነበር ከተቀመጥኩበት የተነሳሁት፡፡ ወደ እቤት ስገባ እማዪ ቁርስ ሰርታ ጨርሳ አቀራርባ ነበር አንድበላ የጠራችኝ በዛች በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ከ እኔ እና ከ እማዪ ወጪ የሚኖር ሰው የለም የቤታችን ግቢ አነስ ያለና ጠባብ የሚባል አይነት ነው የዛሬን አያርገውና ሙና ይህቺ ጠባብ ግቢያችን ፅድት አድርጋ ትይዘው ስለነበር ሰፊ ግቢ ካላቸው ሰዎች በተሻለ ያምር ነበር ሙኒ አበባ መትከል እነሱን መንከባከብ በጣም ያስደስታታ ነበር በዚች በጠባብ ግቢ ላይ በግራና ቀኝ በጣሳ በጣሳ ተደርገው የተቀመጡ አበባዎች አሉ በእርግጥ አበባዎቹ ለግቢው ውበት ቢሰጡትም በዛ ከተባለ አምስት ሰው ብቻ የማሚያቆም ቦታ ነው ያለው ስለግቢያችን እያወራሁ አደከምኳቹ አይደል እና ካቆምኩበት ልቀጥልና እማዬ የሰራችውን ቁርስ ድብን አድርጌ ከበላሁ በኃላ የበለሁበትን እማዬ እንድታነሳው ትቼላት ተነሳሁ በነገራችን ላይ እማዬ ምንም አይነት ምግብ ብትሰራ ሁሌም ቢሆን እየጣፈጠኝ ጥርግ እድርጌ ነው የምበለው እንዲህ ሲሆን እማዬን ደስ ይላታል ለ ነገሩ ባይላትም እማዬ የሰራችውን ምግብ መተው አያስችለኝም ፡፡

ከጓደኞቼ ጋር በጠዋት ለመገናኘት ተነጋግረን ስለነበር ቁርስ ከበላሁ በኀላ ፀጉሬን ወደ ሳሎን ቤት ከመግቢያው በር ጎን በተንጠለጠለው መስታወት ሳየው ቆሽሿል የብርድ ልብስ የተነጫጨ ስላለው ጓደኞቼ ጋር ከመሄዴ በፊት ታጥቤ ልፈርዘው ብዪ ወደ መኝታ ቤታችን ገባሁ ....
ሁል ግዜ እኔ የምጠቀምባቸውን እቃዎች በስርአቱ አላስቀምጥም እማዬ ሁል ግዜ ነው የምትቆጣኝ አቃህን በስርአቱ አስቀምጥ እያለች ትናገረኛለች ግን ልምድ ሆኖብኝ ነው መሰል አንድም ቀን በስርአቱ አስቀምጬ አላውቅም ፡፡ ዛሬም ጄሌን የት እንዳስቀመጥኩት አላውቅም መኝታ ቤቱን እየዞርኩ ፈለኩኝ ግን አላገኘሁትም ወደ ሳሎን ቤት ሄጄ እማዬን ስጠይቃት እንዳላየችው ነገረችኝ ምን ላድርግ እንዳልተወው ፀጉሬ ቆሽሿል ከታጠብኩ ደግሞ የግድ ጄል መቀባት አለብኝ የኔ ፀጉር ጄል ካልተቀባሁት በጣም ነው የሚያስጠላው ከመፈለግ ውጪ ሌላ ምርጫ ስላልነበረኝ በድጋሚ ለመፈለግ ወደ መኝታ ቤት ገብቼ መፈለጌን ተያያዝኩት አሁንም ላገኘው አልቻልኩም ሁሉም ቦታ ፈልጌ ሳጣው በቃ ልተወው ብዬ ልወጣ የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ ስደርስ ለካ አልጋው ስር አልፈለኩም ብዪ ተመልሼ ወደ ወስጥ ገባሁ በጉልበቴ ተንበርክኬ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጄን ወደ አልጋው ስር ልኬ ጄሌን ስፈልግ እጄ የሆነ በፌስታል የታሰረ እቃ ላይ አረፈ በእጄ ስነካው ትንሽ ጠጠር ያለ ነገር እን መፅሀፍ ነገር ይመስላል ምን እንደሆነ ለማወቅ ስለፈለኩ ፌስታሉን በእጄ እየጎተትኩ ከ አልጋው ሰር አወጣሁት ፌስታሉ አቧራ ብቻ ነው አቧራውን በእጄ እንደ ማራገፍ አድረጌ የተቋጠረውን ፌስታል ለመፍታት መታገል ጀመርኩ በጣም ጠብቆ ስለታሰረ በቀላሉ መፍታት አልቻልኩም ታግዬም ቢሆን በመጨረሻ ፈታሁት ፌስታሉ ውስጥ ሁለት መካከለኛ የሆኑ የህይወት ታሪክ መፃፊያ (ዲያሪ) ደብተሮች አሉ የማን ነው ብዪ ለመክፈት ስሞክር በቁልፍ ተቆልፎዋል ፡፡ መክፈት አልችልም ማለት ነው ግን የሰው ሚስጥር ማየት ምን ያደርግልኛል ብዬ እንደመጀመሪያው ፌስታል ውስጥ ከተትኩት እውነት ለመናገር የማን እንደሆነ ለማወቅ እና ለማየት በጣም ጓጉቻለሁ ግን ተቆልፋል ሲያናድ ቁልፉ ባይኖር ኖሮ አነበው ነበር ቁልፋን ለመስበር ስታገል እማዪ ከመጣች ስለምትቆጣኝ ነው የተውኩት እማዪ ከቤት ስትወጣ እሰብረዋለሁ ብዪ እዛው አልጋው ስር መለስኩት ፡፡ አገኘኃው እንዴ አለችኝ እማ ሳሎን ቤት ውስጥ ሆና እኔ ምን እየፈለኩ እንደነበር እራሱ እረስቼዋለሁ ሀሳቤ እንዳለ ፌስታሉ ላይ ስለነበር ምኑን ብላትስ ለእማዬ.....
.. አንተ ቀልበ ቢስ ምኑን ትለኛለህ እንዴ ልትፈልገው የገባኧውን ነዋ... ስሙ ምን ነበር ይሄ ለ ፀጉርህ የምትቀባውን ስትለኝ ጄል ልፈልግ እንደ ገባሁ አስታወስኩ እውነትም ቀልበ ቢስ ነኝ..

... አንዳላገኘሁት ለእማዪ ነግሪያት መኝታ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ አማራጭ ስላጣሁ ፀጉሬን በጠር በጠር አድርጌ በትንሽዬ ቅባት ነካክቼ ወጣሁ ጓደኞቼን አግንቼ ትንሽ ካወራን በኃላ እኔ ስለደበረኝ ወደ ቤት ተመለስኩ እንደ አጋጣሚ ሆኖእቤተት ስደርስ እማዬ እቤት አልነበረችም ፡፡ ቤቱ አልተስተካከለም እነንዳደርንበት ነበር የእማዬን ያህል ባይሆንም ያቅሜን ያህል እያስተካከልኩ ሳለሁ ያ የቅድሙ ፌስታል አስታወስኩ የማስተካክለውን ቤት ትቼ ወደ መኝታ ቤት አመራሁ ፌስታሉን ካስቀመጥኩበት አንስቼ ወስጡ ያለውን ዲያሪ አወጣሁ ፡፡ ቁልፋን ለመክፈት ያሰብኩትን ያህል አላስቸገረኝም በቀላሉ ተከፈተልኝ የዲያሪው የመጀመሪያ ገፅ ላይ በትልቁ በ አልበም ሳያዝ የተለጠፈ የወንድ ፎቶ አየሁ ልጁ ለ አይኔ አዲስ አልነበረም ግን የሱ ፎቶ ያለበት ዲያሪ እኛ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል ?እያልኩ ቀጣዮን ገፅ ገለፅኩ በቀጣዪ ገፅ በስተ ግራ በኩል ዋሌት ፎቶ ተለጥፎዋል ፎቶው የሙና እና የመጀመሪያ ገፅ ላይ የለው ልጅ አብረው የተነሱት ፎቶ ነው፡፡ ሙና ማለት የ አክስቴ ልጅ ናት እኛ ቤት ትኖር ስለነበር አብዛኛው እቃዎቿን እኛ ቤት ነበር የምታስቀምጠው፡፡
ሙና ሁሉም ነገር ሳይበዛ ሳያንስ የተሰጣት ይመስላል ቆንጆ የምትባል አይደለችም ግን አታስጠላም የ ሆነ የሚስብ ነገር አላት ቁመቷ እረጅም አይደለችም አጭርም አትባልም መካከለኛ ቁመት ያላት ናት የፊቷ ከለር ቀይ የሚባል አይደለም ጥቁርም አይደለችም ጠየም ያለች ቸኮሌት ከለር ነገር ነች ፡፡

ሙና እኛ ቤት ውስጥ ከ አስር አመት በላይ ኖራለች ፡፡ግን እንዴት ዲያሪ ስትፅፍ አይቻት አላውቅም ? ሙና የአክስቴ ልጅ ትሁን እንጂ ለ እኔ ልክ እንደ እህት ነበረች መወለድ ቋንቋ ነው አይደል የሚባለው ......
ዲያሪውን ማንበብ ፈልጊያለው ግን ትንሽ ከበደኝ የግሏ ሚስጥር ነው ብዬ ዲያሪውን ወደ ነበረበት መልሼ ወደ ፅዳቴ ተመለስኩ እንደ ነገሩ ቤቱን አፀዳድቼ ጨረስኩ ፡፡ያው እንደምታውቁት ግቢያችን መስተካከል የሚያስፈልገው አይነት አይደለም የወዳደቁትን አቃዎችን አነሳስቼ ወደ ሳሎን እንደገባሁ በስተ ግራ በኩል ባለው ከፍ ተደርጎ በተሰራው የ እንጨት ወንበር ላይ ተቀምጬ ትንሿ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ካንዲ ክረሼን መጫወት ጀመርኩ ግን ቀልቤ እንዳለ ዲያሪው ጋር ነው ቆይ ግን ባነበው ምን ችግር አለው ኧረ ግን የሰውን ሚስጥር ማንበብ ይደብራል እያልኩ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ በመጨረሻም አንድ ውሳኔ ወሰንኩ የ እህቴ አይደል ባነበው ችግር የለውም ብዪ ዲያሪውን ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን ቤት ይዤው መጣሁ በኤል ሼፕ ቅርፅ በተነጠፈው ፍራሽ መሀል ተቀምጬ ማንበብ ጀመርኩ.....

፡ ይቀጥላል

10/01/2018

ማክሰኞ ምሽት ላይ የወጡ ሠፊ የዝውውር ዜናዎች አስተያየቶች እና ሌሎችም አጫጭር ትኩስ የእግር ኳስመረጃዎችን! ያንብቡ - Latest Transfer News Update!ቶሎ-ቶሎ ዜናዎችን እንድናደርሳችሁና ምንም ዜናእንዳያመልጣቹ ከታች Like ማድረግዎን አይርሱ!

አሌክስ ሳንቼዝ በስተመጨረሻ አርሴናል ተሰናብቶ በ£25m ወደ
ማንችስተር ሲቲ ሊያመራ ከጫፍ እንደ ደረሰ ብዙ የሚዲያ አውተሮች
በሰፊው እየዘገቡ ይገኛሉ The Sun ዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ ለብራዚላዊው Lucas Moura ያቀረበውን £25m
በPSG ቤት ተቀባይነት መግኛቱን Telefoot ዘግቧል።

የቶትንሃም የክንፍ መስመር ተጫዎች N'koudou በውሰት ለአንድ አመት
ለበርንሌ አሳልፎ ሰጧል sky Sport ዘግቧል።

ወስትሃም ዩናይትድ የኒውካስትል ተከላካይ jonjo Shelvey በ£12m
ሊያስፈርሙ ከጫፍ መደርሳቸውን ታውቃል Daily Express ዘግቧል ።

አርሴናል የሳንቼዝን ቤታ ሊታካላቸውን የምችለውን ተጫዎች Cristian Pavón's በ£37m ሊስፈርሙ ከጫፍ እንደደረሱ daily ዘግቧል።


አንድሬስ ክሪስቲንሰን ከቼልሲ ጋር ለ4 አመት ከግማሽ አዲስ የሚያቆየውን የውል ስምምነት ተፈራርሟል ።

ቺሊ የቀድሞውን የኮሎምቢያ አሰልጣኝ ሪየናልዶ ሩዳን እስከ 2022 የዓለም ዋንጫ ድረስ አዲስ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አድርጋ መቅጠሯን በይፋ ገልፃለች።

11/12/2017

አርዕስተ ዜና:
የብሪታኒያው ኬፊ የማዕድን ኩባንያ በኢትዮጵያ በወርቅ ማውጣት ዘርፍ ሊሰማራ ነው
በቻምፒየንስ ሊጉ ቼልሲ ከባርሴሎና ማድሪድ ደግሞ ከፒ ኤስ ጂ ተገናኝተዋል
በቻምፒየንስ ሊጉ ቼልሲ ከባርሴሎና ማድሪድ ደግሞ ከፒ ኤስ ጂ ተገናኝተዋል
туристический онлайн-справочник
Лучшие Андроид планшеты
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 2 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ከየምድባቸው አንደኛና ሁለተኛ የወጡ ቡድኖችን በሚያገናኘው የጥሎ ማለፍ ድልድል ታላላቆቹ የስፔን ክለቦች ከባድ የሚባል ድልድል ደርሷቸዋል።

የአንቶኒዮ ኮንቴውን ቼልሲ ከስፔኑ ባርሴሎና ያገናኘው ድልድልም ተጠባቂ ሆኗል።

ሌላው የስፔን ክለብና የውድድሩ ባለ ክብረወሰን ሪያል ማድሪድ ጠንካራውን ፒ ኤስ ጂን ያስተናግዳል።

ሁለቱ ጨዋታዎች በጥሎ ማለፉ ከባድና ተጠባቂ ሆነዋል።

በሌሎች የጥሎ ማለፍ ድልድሎች የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ከእንግሊዙ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ተገናኝቷል።

የስዊዘርላንዱ ባዜል ደግሞ በፕሪሚየር ሊጉ አልቀመስ ያለውን ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

የፖርቹጋሉ ፖርቶ ከሊቨርፑል ሲደለደል፥ የስፔኑ ሲቪያ ደግሞ ከማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ ተገናኝቷል።

ሻክታር ዶኔስክ ከጣሊያኑ ሮማ እንዲሁም ባየር ሙኒክ ከቤሺክታሽ ሌሎች የጥሎ

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Riyadh?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Riyadh