Zinq Sport - ዝንቅ ስፖርት

Zinq Sport - ዝንቅ ስፖርት

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Zinq Sport - ዝንቅ ስፖርት, Sports, 1400 Andrews Pkwy, Allen, TX.

07/11/2025

ሄንደርሰን ብሬንትፎርድን ሊቀላቀል ተስማማ!

እንግሊዛዊው አማካይ ጆርዳን ሄንደርሰን የፕሪምየር ሊጉን ክለብ ብሬንትፎርድን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። ከአያክስ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ኮንትራት የሌለው ሄንደርሰን፣ ብሬንትፎርድን በነፃ ዝውውር ይቀላቀላል።

የ35 ዓመቱ አማካይ ሄንደርሰን ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በመመለስ የሁለት ዓመት ውል እንደሚፈርም ተነግሯል። ሌሎች የዝውውር አማራጮች ቢቀርቡለትም፣ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመመለስ በመወሰኑ ብሬንትፎርድ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ተቃርቧል።

የዝውውሩ ሂደት ቢጠናቀቅም፣ ጆርዳን ሄንደርሰን ለቀድሞ የቡድን አጋሩ ዲያጎ ጆታ ክብር ዝውውሩ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንዲደረግ መጠየቁ ተዘግቧል።

ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/11/2025

"የክለቦች ዓለም ዋንጫ ያስፈልጋል" - ቬንገር

የቀድሞው የፈረንሳይ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር አስፈላጊነት እንደሚያምኑ ገለጹ።

በቅርቡ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለውድድሩ መጀመር ባቀረቡት ትችት ላይ ምላሽ የሰጡት ቬንገር፣ "የውድድሩ ደጋፊ ነኝ" ብለዋል። የቀድሞው የአርሰናል ታሪካዊ አሰልጣኝ አርሴን ቬንገር በአሁኑ ወቅት የፊፋ ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዕድገት ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።

"የክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር ያስፈልጋል" ያሉት ቬንገር፣ እዚህ የነበሩትን ሁሉንም ክለቦች ብትጠይቁ በድጋሚ መወዳደር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ውድድሩ በደጋፊዎች ስለመወደዱ አንስተውም፣ "የተመልካች ቁጥር ዝቅተኛ ነው ተብሎ ቢገመትም ከፍ ብሎ ታይቷል፤ ምላሹ ይሄ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/10/2025

"ማሸነፍ ይገባናል" - ሀኪሚ

የፒኤስጂው የመስመር ተጫዋች አሽራፍ ሀኪሚ፣ ቡድናቸው በሪያል ማድሪድ ላይ የተቀዳጀው ድል እንደሚገባቸው ተናግሯል።

"ጨዋታውን ስላሸነፍን ጥሩ ስሜት ላይ ነን፤ ጨዋታው በሙቀቱ ምክንያት አስቸጋሪ ነበር፣ የገጠመን ጠንካራ ቡድን ነው" ሲል ሀኪሚ ከጨዋታው በኋላ ገልጿል።

አክሎም፣ "በየትኛውም ቦታ እንድጫወት ነፃነት ስለተሰጠኝ ደስተኛ ነኝ፤ እኔ ወደፊት በምወጣበት ጊዜ ቦታውን የሚሸፍኑ የቡድን አጋሮቼን አመሰግናለሁ" ብሏል።

ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/08/2025

ራሽፎርድ ካሪንግተን ታየ!

ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ተመልሶ በካሪንግተን የልምምድ ማዕከል ሪፖርት አድርጓል።

ራሽፎርድ አዲስ ክለብ እንዲያፈላልጉ ጊዜ ከተሰጣቸው ተጫዋቾች አንዱ ሲሆን፣ ሰኞ እና ማክሰኞ በካሪንግተን ተገኝቷል። በልምምድ ወቅትም የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ስብስብ ሳይቀላቀል በግሉ እንደሰራ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ትላንትና የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን፣ ራሽፎርድን ጨምሮ በቡድኑ የማይፈለጉ አምስት ተጫዋቾች የወደፊት ቆይታቸውን እንዲወስኑ የመመለሻ ጊዜያቸውን ማዘግየቱ ይታወቃል።

ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/08/2025

"ዮኬሬሽ በትልቅ ሊግ አልታየም!" - ሪዮ ፈርዲናንድ

የቀድሞው የእንግሊዝ ኮከብ ሪዮ ፈርዲናንድ፣ አርሰናልን ሊቀላቀል የተቃረበው ቪክቶር ዮኬሬሽ በትልቅ ሊግ ራሱን አላሳየም ሲል ተናግሯል። ፈርዲናንድ የፖርቹጋል ሊግን ቢያከብርም ትልቅ አለመሆኑን ገልጿል።

"ስለዚህ ዮኬሬሽ ለፕሪምየር ሊግ ክለብ ከፈረመ ማንነቱን ማሳየት አለበት፤ እስካሁን በትልቅ ሊግ ስኬት አላሳየም" ብሏል።

ስዊድናዊው አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ አርሰናልን ሊቀላቀል ከጫፍ ደርሷል።

ይህን እና ሌሎችንም አዳዲስ የስፖርት ዜናዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/08/2025

ባየር ሙኒክ ንኩንኩን ለማስፈረም በድጋሚ ማለሙ ተገለፀ!

የጀርመኑ ቡንደስሊጋ ክለብ ባየር ሙኒክ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጫዋች ክሪስቶፈር ንኩንኩን ለማስፈረም በድጋሚ ኢላማ ማድረጉ ተዘግቧል። የቡንደስሊጋው አሸናፊ ባየር ሙኒክ ባለፈው አመት ተጫዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ አድርጎ እንዳልተሳካለት ይታወሳል።

በዚህ ክረምት ኢላማ ያደረጓቸውን ፍሎሪያን ቨርትዝ እና ኒኮ ዊሊያምስን ማጣታቸውን ተከትሎ፣ ባየር ሙኒክ ንኩንኩን ወደ ጀርመን ለመመለስ እንደሚፈልግ ተዘግቧል። ቼልሲ በበኩሉ ተጫዋቹን ለመሸጥ የሚፈልገው በቋሚ ዝውውር ብቻ መሆኑን ገልጿል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/07/2025

የዌስትሀም ደጋፊዎች በኩዱስ ዝውውር ላይ አድማ ሊጠሩ ነው!

የዌስትሀም ዩናይትድ ደጋፊዎች ማህበር ክለቡ የፊት መስመር ተጫዋቹ መሐመድ ኩዱስን ለቶተንሀም እንዳይሸጥ ጠይቋል። ደጋፊዎቹ ክለቡ ተጫዋቹን ለቶተንሀም አሳልፎ የሚሰጥ ከሆነ አድማ ለመጥራት እና ተቃውሞ ለመቀስቀስ እየተዘጋጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ቶተንሀም ሆትስፐር ኩዱስን ከዌስትሀም ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆኑ ይታወቃል። መሐመድ ኩዱስ በበኩሉ ቶተንሀም ያቀረበለትን ጥያቄ ተቀብሎ ይሁንታውን መስጠቱ ተዘግቧል። ቶተንሀም ለተጫዋቹ ያቀረበው 50 ሚሊዮን ፓውንድ ውድቅ የተደረገ ሲሆን፣ በዚህ ሳምንት አዲስ የዝውውር ሂሳብ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/07/2025

"ራሽፎርድ ዩናይትድ እንዲቆይ እፈልጋለሁ" - ሁዋን ማታ

የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ሁዋን ማታ፣ ማርከስ ራሽፎርድ በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት ቢቆይ ለሁለቱም ወገኖች የተሻለ እንደሆነ ተናግሯል። ማታ፣ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ውሳኔያቸውን በጥንቃቄ መመዘን እንዳለባቸው እና ራሽፎርድን በቡድኑ ውስጥ እንዲያስቀሩት ጥሪ አቅርቧል።

ማታ በዩናይትድ በነበረው ቆይታ ከራሽፎርድ ጋር ከ100 በላይ ጨዋታዎችን አብሮ ተጫውቷል። ራሽፎርድ ከዋናው ቡድን ጋር ልምምድ ሲጀምር ለእሱ ልዩ ፍቅር እንደነበረው የገለጸው ማታ፣ "እሱ ያለፍርሃት ነበር የሚጫወተው፣ ድንቅ ነበር" ብሏል።

ማታ አክሎም፣ "እንደ ማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊ እና የራሽፎርድ ጓደኛ፣ እሱ እዛው ቆይቶ እንዲሳካለት እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም የልጅነት ክለቡ ነው። አሁን ምን እየተፈጠረ እንዳለ አላውቅም፣ ነገር ግን እሱ ቢቆይ እና ደስተኛ መሆን ከቻለ ለሁለቱም ጥሩ ጥቅም ይመስለኛል" ሲል ተደምጧል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/07/2025

ዩናይትድ ለፈርናንዴዝ እና ዳሎት እረፍት ሊሰጥ ነው!

ማንቸስተር ዩናይትድ ለፖርቹጋላውያን ተጫዋቾቹ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ዲዮጎ ዳሎት ተጨማሪ እረፍት ሊሰጥ ነው ተብሏል። ሁለቱ ተጫዋቾች በቅርቡ በዲያጎ ጆታ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ከተገኙ በኋላ በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መግባታቸው ተዘግቧል።

ይህን ተከትሎም ሰን ስፖርት እንደዘገበው፣ ዩናይትድ ተጫዋቾቹ ተጨማሪ አንድ ሳምንት አርፈው ወደ ልምምድ እንዲመለሱ ፈቅዷል። የቡድኑ ተጫዋቾችም ለእነሱ ድጋፍ እያሳዩ እንደሆነ ተመላክቷል። ከእረፍቱ በተጨማሪ ተጫዋቾቹ የስነ-ልቦና ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ተገልጿል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/07/2025

ቼልሲ ኒኮላስ ጃክሰንን ለመሸጥ አቅዷል?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በዚህ ክረምት ሴኔጋላዊውን አጥቂ ኒኮላስ ጃክሰንን በንቃት ለመሸጥ እየሰራ እንዳልሆነ ተገልጿል። ሆኖም ሰማያዊዎቹ ለጃክሰን ጥሩ የዝውውር ሂሳብ ከቀረበላቸው፣ ነገሩን ለመመልከት ዝግጁ መሆናቸው ታውቋል።

በአሁኑ ወቅት በርካታ ክለቦች ኒኮላስ ጃክሰንን ለማስፈረም ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተዘግቧል። የ23 ዓመቱ አጥቂው በቼልሲ ቤት ለዘጠኝ ዓመታት የሚቆይ ኮንትራት እንዳለውም ይታወቃል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/06/2025

ኦላ አይና ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር አዲስ ውል ተፈራረመ!
የቀኝ መስመር ተከላካዩ ኦላ አይና ከኖቲንግሀም ፎረስት ጋር እስከ ሰኔ 30፣ 2028 የሚያቆይ የሶስት አመት አዲስ ውል መፈራረሙ ተገለጸ።

ናይጄሪያዊው ተጫዋች አይና ከቶሪኖ ጋር ውሉ ካለቀ በኋላ በጁላይ 2023 በአንድ አመት ኮንትራት ፎረስት መቀላቀሉ ይታወሳል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በድምሩ 59 ጨዋታዎችን አድርጎ 3 ጎሎችን ሲያስቆጥር፣ 2 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል።

ባለፈው 2024/25 የውድድር ዘመን አይና በሁሉም ውድድሮች 37 ጨዋታዎችን ያደረገ ሲሆን፣ ፎረስት የፕሪሚየር ሊጉን በሰባተኛ ደረጃ ሲያጠናቅቅ እና የኤፍኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ መድረስ ችሏል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

07/06/2025

"ዙቢሜንዲ ለቡድኑ ትልቅ አቅም ይጨምራል" - አርቴታ

የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አዲሱ ፈራሚያቸው ማርቲን ዙቢሜንዲ ለቡድኑ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገለጹ። አርቴታ "ዙቢሜንዲ ለቡድኑ ጥራት እና ትልቅ የእግር ኳስ እውቀት ይጨምራል" ብለዋል።

አሰልጣኙ ዙቢሜንዲ የጨዋታውን ሂደት የመረዳት እና የመተንተን አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፣ ይህ ችሎታው የቡድኑን አቅም እንደሚያሳድግ አስረድተዋል። አርቴታ አክለውም "ተጨዋቹ ለቡድናችን በትክክል ይስማማል፤ የቡድኑ ቁልፍ ተጫዋች የሚያደርገው ሁሉም ባህሪ አለው" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የበለጠ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.me/+Oe6AIBLwdZE0MDNk

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in Allen?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


1400 Andrews Pkwy
Allen, TX
75002