05/12/2026
ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ዜና !!
አትሌት የብርጓል መለስ በድንገት ከዚህ አለም ድካም አረፈች!!
አትሌቷ የሁለት ልጆች እናትም ነበረች!!
የ5 አመት ልጅ እና የ3 አመት ልጅ እናት የሆነችው የማራቶን አትሌቷ የብርጎል መለስ ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት ድረስ የአለማችን 91ኛዋ ፈጣን የማራቶን አትሌት ነበረች 54 ኢንተርናሽናል ውድድሮችን አድርጋ 3 ጊዜ ሀገሯን የወከለችው የብርጓል መለስ በ2013 በፖላድ በተካሄደው የአለም ሀገር አቋራጭ ውድድር በቡድን ሀገራችን የብር ሜዳሊያ ስታገኝ የብድኑ አባል ነበረች።
በአለማችን ላይ በሚታወቁ ትላልቅ ማራቶኖች እና ግማሽ ማራቶኖች ላይ ከፊት የማናጣት ጀግናዋ አትሌት የብርጓል መለስ ከቅርብ ጊዜ ወዲይ በልምደ ላይ ድንገት ስልምልም ብሎ የመወደቅ አደጋ በተደጋጋሚ እያገጠማት እንደነበረና ዛሬም በዚሁ አይነት ሁኔታ ህይወቷ እንዳለፈ ለማረጋገጥ ችያለሁ።
አትሌት የብርጓል መለስ ህይወቷ እስካለፈበት ሰዓት ድረስ በጎዳና ላይ ሩጫዎች ትታወቅ ነበረ ያረገጣቻቸው የአለማችን ጎዳናዎች አልነበሩም።
22 ማራቶኖች
19 ግማሽ ማራቶኖች
5 ጊዜ 10k በመሮጥ የምታወቅ ሲሆን ትራክ የሮጠችው 2 ጊዜ በ10,000ሜ ብቻ ነበረ ቀሪ የሀገር አቋራጭ ውድድሮች ናቸው። ጠቅላላ ውድድሮቿን ከ75 % በላይ በደረጃ የጨረስ ጠንካራ አትሌት ነበረች።
1 ሜትር ከ64 ሳ ሜትር ቁመት
55 ኪሎ ግራም ትመዝን የነበረችው ጀግናዋ አትሌት የብርጓል 37ኛ አመት ሊሞላት 24 ቀን ሲቀር ከዚህ አለም ድካም አርፋለች።
ነፍስ ይማር!!
05/11/2026
በዚህ ሳምንት ከፍተኛ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አመራሮች፦ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን (World Athletics) ዋና ሥራ አስፈፃሚ (CEO) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጡ ነው ይላል ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ገፅ ያገኘነው መረጃ
በዚህ ሳምንት ከሚመጡት ከፍተኛ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አመራሮች፦ውስጥ
1. ጆን ሪጅን - የዓለም አትሌቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
2. ማርክ ሁርስት - የዓለም አትሌቲክስ የጨረታ፣ የውድድር እና የዝግጅት ክፍል ኃላፊ
ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአዲስ አበባ በመገንባትና በመስፋፋት ላይትን የአትሌቲክስ መሠረተ ልማቶችን ይጎበኛሉ ይላል መረጃው
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጣይ ልታስተናግዳቸው በጠየቀቻቸው ዓለም አቀፍ ውድድሮች ዙሪያ ከተለያዩ የመንግሥት እና የፌደሬሽኑ አመራሮች ጋር እንደሚወያዩ ፌደሬሽኑ ገልፆል ።
ይህ ጉብኝት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ መድረክ ያላትን ከፍተኛ ስፍራ የሚያጠናክር እና ወደፊት ትልልቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም የሚያሳይም ነው ተብሏል።
Photo google
05/11/2026
በፎቶው ላይ ከምትመለከቷቸው ውስጥ በ2021 ኬኒያ ላይ በተካሄደው U20 ኢትዮዽያን ወክለው ወርቅ ካስገኙት አትሌቶች እነማንን ያስታውሳሉ?
05/11/2026
በቅርቡ የተሞሸረው አትሌት ቦኬ ድሪባ በማራቶን አሸነፈ!!
በሞሮኮ ራባት በተደረገ የማራቶን ውድድር በወንድም በሴትም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።
በሞሮኮ ራባት በተደረገ የማራቶን ውድድር ነው በቅርብ ከአትሌት ሲንቦ አለማየሁ ጋር የተሞሸረው ቦኬ ድሪባ አሸናፊ የሆነው።
በሴቶች ከ3 አመት በኋላ ወደ ውድድር የተመለችው የ32 አመቷ አለምፀሀይ አሰፋ አሸናፊ ሆናለች።
MEN:
1. Boki Diriba 2:07:52
2.Tolcha Tefera 2:08:27
3. Chalu Deso 2:08:28
WOMEN:
1Alemtsehay Asefa 2:25:03 2Meseret Abebayhu 2:25:42
3Siranesh Yirga 2:27
የተወሰኑ ፎቶዎች ከኤሊት አትሌት ገፅ ተጠቅመናል።
05/11/2026
ዛሬ የአትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት ልደት ነው!!
አትሌቱ ኦሎፒያን ነው!!
የመስፍን ኢንጅነሪግ ክለብ አትሌት ነው!
አትሌቱ በኢንተርናሽናል ደረጃ 112 ውድድሮችን አድርጓል።
በተደጋጋሚ ብዙ የሮጠው 5000 ሜትርን ነው 57 ጊዜ ሮጣታል።
በ5ሺ ሜ የምንጊዜም የዓለማችን ፈጣን ባለሰዓቶች ውስጥ ያለው ደረጃ ስናይ፦ የዛሬ 2 አመት በ30 ሜይ 2024 በኖርዌይ ኦስሎ ያስመዘገበው
12:36.73 NR ሰዓቱ በ2ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጎታል።
➙ 18 ጊዜ ሀገሩን ወክሏል።
በሀገር ውክልና ውድድር ማለትም በኦሊምፒክ ፤ በአለም የአትሌትክስ ሻምፒዮና ፤ በወጣቶቸ ሻንፒዮና ፤ በሀገር አቋራጭ ውድድሮች እንዲሁም በአፍሪካ ሻንፒዮናዎች በጠቅላላው 3 ወርቅ 1 ብር 2 ነሀስ በቡድን 2 ወርቅ በጥቅሉ 8 ሜዳሊያዎችን ለሀገሩ አስገኝቷል።
አንድ አትሌት በሩጫ ዘመኑ ሊያሳካ ከሚገባው አንዱና ዋናው በኦሊምክ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍና ሜዳሊያ ማጥለቅ ነው ይህ አትሌት በኦሊምፒክ ተሳትፎው በ2016 በሪዮ ኦሎፒክ በ5000ሜ የነሀስ ሜዳሊያ አጥልቋል።
ኢትዮራነርስ ለኦሊምፒክ ጀግኖች ትልቅ ክብር አለው!
ዛሬ የጀግናው አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት ልደት ነው። አትሌቱ በዛሬዋ ቀን እ ኤ አ 11 May 1994 ዓ ም ተወለደ። 32 አመት።
Happy Birthday!
መልካም ልደት!
እንኳንም ተወለድክ!!
የሀጎስ አድናቂ የሆነችሁ በሙሉ እስኪ እንኳንም ተወለድክ በሉት!!
ሀጎስ ልደቱን ሲያከብር የሚያሳይ ቪዲዮ ዮቱባችን ላይ ተጭኗል ሰብስክራይብ አድርገው ይመልከቱ።
ሼር ብቻ!
05/10/2026
የአትሌቶች የቪዛ ጉዳይ መፍትሔው ምንድን ነው?
በዚህ ጉዳይ ይረፋ ብርሀኑ የተሰጠ የመፍትሄ ሀሳቦች!!
ኮመንት ላይ ይመልከቱ
05/10/2026
https://www.youtube.com/live/DCw8i_CAm6k?si=irIW2uF_zZmJZEQ8
የአትሌቶች የቪዛ ጉዳይ መፍትሔው ምንድን ነው? በዚህ ጉዳይ ይረፋ ብርሀኑ ምን ይላል?Send a message...
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.