Tsega Muche's Page የፀጋ ሙጬ ገፅ

Tsega Muche's Page  የፀጋ ሙጬ ገፅ

Share

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም በክብር ትኑር

12/28/2024
10/18/2022

____እንዳፈሩ ዝራ____
ይህ ስራ አማርኛ ቋንቋ ለሚገባው ሰው ሁሉ በስጦታ የተሰጠ ነው
ፀጋ ሙጨ።

ሙሉ ጎጃም MuluGojam Tsega Muche EmmaHulu vol8 07/23/2022

_____ሙሉ ጎጃም_____
በፀጋ ሙጬ
እግዚአብሔር ሁልጊዜም መልካም ነው
እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቸ አላችሁ ወይ?
እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ዛሬም አለሁ
እስኪ ሁላችሁም AMREN TUBE ሰብስክራይብ አድርጉና ብዙ ስራየ ለህዝብ እንዲደርስ አግዙኝ
ህይወት መምጫ ወይም መግቢያ እንጅ መሄጃ ወይም መመለሻ የላትም
ስለዚህ ትናንት ሞክረህ ያልተሳካልህ ነገር ሁሉ በዛሬ መነፅር ወይም በዛሬ መስታወት ሲታይ ትክክል ነው
እንኳንም ይትናንት ሙከራየ ያልተሳካልኝ
ትናንት ግን ጥረቴ ባለመሳካቱ ልፋቴ ባለመሟላቱ አቤት ፈጣሪን እስከ መርገም ደርሸ ነብርኮ!!!!!! የለህም እስከማለትም ደርሸ ነበር
ዛሬን ሆኘ ሳየው ግን ለካ ለበጎ ነው ፈጣሪ ይቅር በለኝ እንኳንም ያልተሳካልኝ ትናንት ቢሳካልኝ ኖሮ የዛሬ ስኬት ላይ አልደርስም ነበር ይቅር በለኝ የሚያስብሉ የብዙዎቻችን የህይወት ተሞክሮዎች አሉ
ኢትዮጵያ ወርቅ ነች
ይችን ወርቅ ለማወቅ በዕሣት ቀልጦ መውጣት ግድ ይላል
ኢትዮጵያዊነትን እንደ አንድ ሀገር ዜግነት የማንቆጥርባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ ግን እንዲህ እንዲህ ብለን ብንናገር ሰሚ አይኖርም ወልደሽ እየው እንደሚሉት የእናቶቻችን እርግማን መሰል የቁጭት ቃል እመስለዋለሁ
ዛሬ ኦሮሞ/አማራ/ትግሬ/ዶርዜ ወዘተ ነኝ ብለን ደረታችንን ነፍተን በሰፈራችን ደምቀን በኢትዮጵያዊነታችን ኮርተን እንዳንታይ የስፌታችን ሰበዙ የጥልፋችን ክር መምዘዙ የንግግራችን ወዙ ግራ አጋብቶን ስንሰቃይ እንታያለን
ኪነጥበብ ብንል ወሎ ተወልደን ወሎ እንደምንሞት እርግጠኖች ሆነን መወለድ እንጅ መሞት የት እንደሚሆን ለሚያውቀው ጌታ ስልጣኑን መስጠት ሲገባን እኛው ፍጡርም ፈጣሪም ሆነን በቃ ወሎ የተወለደ ወሎ ይሞታል ብለን ወስነን ቲክቶኩ ፌስቡኩ ዩቱቡ እሱን ብቻ ሲደጋግም
ስፖርት ብንል አማራን በማንነቱ ምክንያት ሆን ተብሎ ቀድሞ እንዳይገኝ አንደኛ እንዳይወጣ አሯሯች አደረጉት ክክክክክክክክክክክክክ የሚል ትልቅ ስም ያለውን አማራ እያየን እንዴት እንግባባ?
ለትችትም ለአድናቆትም መሰረት የሌለን ማርያምን ስንገርም
አረወዲያልኝ እቴ ዘንድሮስ የመጨረሻው ነው አሉ እትየ ይመናሹ ክክክክክክክክክ እንዳው ከማን ጋር እንኑር ከማን ጋር እንግባባ?
ኢትዮጵያ ወርቅ ነች
ጎጃም ደግሞ ሰምና ወርቅ ነች
ደሞ በዚህም ቅና አሉህ እንግዲህ ክክክክክክክክክ ጎንደርስ? ወሎስ? ኦሮሞስ? እሱን ደግሞ አንተ ጨምር ለኔ የታየኝ ለጊዜው ኢትዮጵያ ወርቅ ነች
ጎጃም ደግሞ ሰምና ወርቅ ነች ብያለሁ ለምን? ካልህ ተመራመር ታሪክ ፈትሽ እኔን አትተይቀኝ
ግን አደራህ እውነት በመናገሬ UNSUBSCRIBE እንዳታደርገኝ ክክክክክክክክክ ጦሜን እንዳታሳድረኝ
ኦህ ለካ ራቴን በልቻለሁ ለዚህ ነው ደረቴን የነፋሁት
ወገኖቸ በማርያም ስንተችም እንዳው ቢያንስ ለህሊና በሚመጥን ሁኔታ እንተች
አማራን አማራ በመሆኑ ምክንያት ስንት በደል እየደረሰበት ስለሆነ ሁላችንም ተደራጅተን ይህን ግፍ እናስቁም እንከላከል ያስማማኛል
ሁላችሁም እንደምታውቁት ብቻየን አንድም አማራ አይዞህ ሳይለኝ ኡኡኡኡ እያልሁ እንደሆነ የምታውቁት ሀቅ ነው
ግን አማራ ለስፖርት ውድድር ዩጂን ኦሪገን አሜሪካ ተልኮ በአማራነቱ ምክንያት ብቻ አሯሯጭ ተደረገ ብሎ ደራርቱን ወይም ፌዴሬሽኑን ለመወንጀል መሞከር ግን የዕውቀት ልዕልናም የብሄርተኝነት ጥግም አይደለም
ሲጀመር እንደ ሀገር ለውድድር የሚላኩ ቡድኖች ማናቸውም ሲያሸንፉ የምትከብረው ሀገር ነች ምክንያቱም ይሄ ዳይመንድ ሊግ አይደለም
ሲቀጥል የቡድን ስራ ሲሰራ አንዴ አንዱ ያሯሩጣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይቀድማል የበረታው አንደኛ ይሆናል እንጅ እዚህ ላይ ዘር የለም
ስም አልጠራም ግን ማርያምን አዝኛለሁ ቢያንስ እንደ ምሁርም እንደ ባለታሪክም አይሁን እንደ አንድ አማራ ኢትዮጵያዊ ግን ወድቀናል
ይህም ብቻ አይደለም
ችግር አለብን ችግራችን ዓለማቀፋዊ ነው ከዚህ ችግር ለመውጣት የችግሩን አስከፊነት አስቀድሞ ተደራጅቶ ለመታገል ብቸኛው መንገድ ደራርቱን የምታህል የኢትዮጵያ መስታወት ከመስደብ የሚጀምር አማራ ባፍንጫየ ይውጣ
ጨርሻለሁ
ጎጃም ብቅ በሉና አንዴ ባባይ ላይ ዋኙ በጣና ገዳማት ተባረኩ ዘጌ ውጡና ከዑራ ኪዳነ ምህረት ጀምራችሁ አድባራትን ጎብኙ ያኔ የህይወት ሚስጥር ይገለጥላችኋል
ህልማችሁ ስራችሁ ሁሉ ፍቅር ክብር ይሆናል የመኖር ቅመም የህይወት ቅኔ ይገለፅላኋል
ከፍ አርጎ አስቀምጧት አምላክ በፀበሉ
በሷ ጠግቦ ያድራል የታችኛው ሁሉ
በጀግኖች መካከል ቆንጆ በሞላበት
አንድ ጎጃም ትኑር ላይነት ለምልክት
ሙሉ ጎጃም ግጥምና ዜማ ፀጋ ሙጬ
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም በክብር ከፍ ብላ ትኑር
ፀጋ ሙጬ ነኝ

ሙሉ ጎጃም MuluGojam Tsega Muche EmmaHulu vol8 EthiopianTraditionalMusic #

03/24/2022

እማ ሁሉ አልበም በቅርብ ቀን

03/24/2022

subscribe our new channel
Amrentube
እማ ሁሉ አልበም በአምረን ቱቢ በቅርብ ቀን።

03/19/2022

visit yeabtsegatube
እማ ሁሉ አልበም በቅርብ ቀን
በ yeabtsegatube
SUBSCRIBE LIKE SHARE
stay connected

Want your business to be the top-listed Gym/sports Facility in SeaTac?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address


17301 32nd Ave S
SeaTac, WA
98188