04/07/2022
ማቲያስ ዴ ላይት ከቼልሲ ይልቅ ባየር ሙኒክን ይመርጣል !
እንደ ስካይ ጀርመን ዘገባ ከሆነ ባየር ሙኒክ ማቲያስ ዴ ላይትን ማስፈረም ይፈልጋሉ።
ዴ ላይት ከ ናግልስማን እና ከክለቡ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግሯል በዚህም ንግግር 22 አመቱ ተከላካይ ደስተኛ ነበር ተብሏል።
ቼልሲ እና ሌሎች ክለቦች ፍላጎት ቢኖራቸውም ዴ ላይት በአያክስ ቆይታው እንኳን እሱን ለማስፈረም ፍላጎት ለነበረው ለ ጀርመኑ ክለብ መፈረም ይፈልጋል።
ባየር ሙኒክ ከጁቬንቱስ ጋር ግንኙነቶችን ጀምሯል ድርድር ጥሩ እድገት ቢኖረውም ለተጫዋቹ ጁቬንቱስ ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚፈልጉ ዝውውሩን አስቸጋሪ ያደርገዋል።
ቼልሲዎች ዴ ላይትን ለማስፈረም ወደ ኃላ አይሉም ምክንያቱም ባየርን ሙኒክ ለተጫዋቹ ከፍ ያለ ወጪ እንደማያወጣ ያምናሉ።
ሆላንዳዊው ተከላካይ ወደ ሙኒክ መሄድን ይመርጣል እና ሁለቱ ክለቦች ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ አድርጓል።
04/07/2022
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2023 ጀምሮ የአፍሪካ ሱፐር ሊግ የሚባል አዲስ ውድድር በታንዛኒያ እንደሚካሄድ አስታውቋል።
04/07/2022
ወደ ሆላንድ ተመልሷል..
በማንቸስተር ዩናይትድ እና በአርሰናል እየተፈለገ የሚገኘው አርጄንቲናዊው ተጨዋች ሊሳንድሮ ማርትኔዝ ወደ አምስተርዳም መመለሱ ተነግሯል። እውቁ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ እንዳረጋገጠው ከሆነ ተጨዋቹ ለአያክስ ክለቡን ለቆ መሄድ እንደሚፈልግ ግልፅ አድርጓል። የማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ቴን ሃግ የተጨዋቹ ፈላጊ ሲሆኑ ተጨዋቹም ከእሳቸው ጋር ዳግም አብሮ የሚሆንበት ዕድል ሰፊ ነው።
04/07/2022
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቻምፒየንስ ሊግ ለመጫወት ከፍተኛ የሆነ የደመወዝ ቅነሳ ለማድረግ ፍቃደኛ ነው፣ ወደ ቼልሲ፣ ባየር ሙኒክ እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜንን ለመቀላቀልም ይስማማል።
07/02/2022
Maneeeeeeeee! Senegallllllll! 🇸🇳 became African Champions for the first time by beating Egypt!
26/10/2021
የግዜ ጉዳይ እንጂ የኦሌ ሶልሻ መባረር አሁን ላይ ዕርግጥ የሆነ ይመስላል ከወዲሁ ክለቡም ከአንዳንድ አሰልጣኞች ጋር መነጋገር መጀመሩ እየተዘገበ ይገኛል..
የማንችስተር ዩናይትድ ቁጥር አንድ ምርጫ ጣልያናዊው አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ሲሆን ዚነዲን ዚዳንን ጨምሮ ሌሎች እጩዎችም በማንችስተር ዩናይትድ ዝርዝር ውስጥ እንዳሉ ዲማርዚዮ ዘግቧል ።
13/10/2021
🏆 ትላንት የተደረጉ የአውሮፓ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች
10/10/2021
🏆🏆 አለም ዋንጫ
🏆🏆 የአውሮፓ ዋንጫ
🏆 ኔሽንስ ሊግ
ፈረንሳይ ሶስቱን የኢንተርናሽናል ዋንጫዎችን ያሸነፈች የመጀመሪያ ሀገር ሁናለች
10/10/2021
ትላንት የተደረጉ የአውሮፓ ሀገራት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ውጤት።
08/10/2021
⚽️ 37’ ካራስኮ አስቆጠረ
⚽️ 40’ ሉካኩ አስቆጠረ
⚽️ 62’ ቤንዜማ አስቆጠረ
⚽️ 69’ ምባፔ አስቆጠረ
❌ 87’ የ ሉካኩ ጎል ተሻረ
⚽️ 91’ ቲዬ አስቆጠረ
ድራማ 👍
08/10/2021
ትናንትና የተደረጉ የአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ውጤቶች!
ዲሞክራቲክኮንጎ 2-0 ማዳጋስካር
ላይቤሪያ 1-2 ኬፕ ቬርዴ
ታንዛኒያ 0-1 ቤኒን
ኢኳቶሪያል ጊኒ 2-0 ዛምቢያ
ናይጄሪያ 0-1 ሴንትራል አፍሪካ
ሩዋንዳ 0-1 ኡጋንዳ
ማሊ 5-0 ኬንያ
ቱኒዝያ 3-0 ሞሪታኒያ